መረጃ

Your internet is very weak.
የእርስዎ ኢንተርኔት በጣም ደካማ ነው።
ናትካ ኢንተርነት ብዙሕ ደካማ እዩ።
nternet kee baaxô daciifa.
በትዕግስት ይጠብቁ!

loading 31-03-2026 06:38am

በሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የመሬት ይዞታ ፋይሎችን በዘመናዊ መንገድ ወደ ዲጂታል የመቀየር ሥራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ።

በሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የመሬት ይዞታ ፋይሎችን በዘመናዊ መንገድ ወደ ዲጂታል የመቀየር ሥራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ። ይህ ፕሮጀክት በዞኑ የሚገኙ ከተሞችን የከተማ መሬት አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ያለመ ነው። የዞኑ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ መኮንን የሱፍ በሥልጠናው ማጠቃለያ እንዳስታወቁት በአንድ ከተማ፣ በሦስት መሪ ማዘጋጃ ቤቶች እና በአንድ ታዳጊ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የከተማ መሬት ይዞታ ፋይሎች በሙሉ ወደ ዲጂታል ተቀይረዋል። ይህም ሥልጠና ሥራው ባልተጀመረባቸው ከተሞች ያለውን የመረጃ አያያዝን ከማዘመን ባሻገር፣ የመሬት ይዞታን በተመለከተ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች እና አገልግሎቶች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል። የዚህ ሥራ መጠናቀቅ፣ የዜጎችን መረጃ የማግኘት መብት እና ሂደት የሚያፋጥን ሲሆን የመረጃ ደህንነት እና ግልጸኝነትን እንዲረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። በቀጣይም ይህንን ስኬታማ ተሞክሮ በመጠቀም በዞኑ የሚገኙ ሌሎች ከተሞችንም በዲጂታል የመረጃ አያያዝ ሥርዓት ለማካተት ዕቅድ መኖሩ ታውቋል። (ወልድያ - ሰሜን ወሎ ዞን ከመልመ መስከረም 12/2018 ዓም)

ይህ ዘገባ የተነበበው 7ጊዜ ነው

Comment Form